Fana: At a Speed of Life!

በሰሜን ሸዋ ዞን በሚገኙ 1ሺህ 128 የምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች ድምጽ እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)  በሰሜን ሸዋ ዞን በሚገኙ 1ሺህ 128 የምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች ድምጽ እየተሰጠ መሆኑን የዞኑ ምርጫ ቦርድ አስተባባሪ ገለጸ።

አስተባባሪው አቶ ሙሉጌታ አክሊሉ ለጣቢያችን እንዳሉት÷በዞኑ ሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ያለ ምንም የቁሳቁስ ችግር ምርጫው እየተካሄደ ነው፡፡

እስካሁን የጎላ ችግር አልገጠመንም ያሉት አቶ ሙሉጌታ ÷መራጩ በሰልፍ እየመረጠ ነው እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ድምጹን እንዲሰጥም አሳስበዋል፡፡

በሰሜን ሸዋ ዞን ከ664 ሺህ በላይ መራጭ የተመዘገበ ሲሆን ሁሉም መራጭ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በመሄድ በቀሪ ሰዓታት ውስጥ እንዲመርጥ ጥሪ ቀርቧል።

የዞኑ ምርጫ አስተባባሪ እንደገለጹት ምርጫው ያለምንም  እንቅፋት እንደቀጠለ ሲሆን÷ ከፖለቲካ ፓርቲዎች የሚቀርቡ ጥያቄዎችን በፍጥነት እየፈታን ነው ብለዋል፡፡

ምርጫው ከምሽቱ 12 ሰዓት ተጠናቆ ቆጠራ እንደሚጀመር ይጠበቃል።

አላዩ ገረመው ከደብረ ብርሀን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.