Fana: At a Speed of Life!

አቶ አወል አርባ ለተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ አሳሰቡ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለዘላቂ ልማት ብሎም ለልማት ሥራዎች ቀጣይነት የተፈጥሮ ሃብትና የአካባቢ ጥበቃ ሥራ ሊጠናከር እንደሚገባው የአፋር ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አወል አርባ አሳሰቡ፡፡

በሁሉም ዞኖችና ወረዳዎች ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ሕዝቡን ባሳተፈ ሁኔታ ለአካባቢ እና ተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ልዩ ትኩረት መስጠት እንደሚያስፈልግ መናገራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

የተፈጥሮ ሃብትንና የአካባቢ ጥበቃ ሥራን ማጠናከር ከአየር ንብረት መጠበቅ ባሻገር በቱሪዝም ዘርፍ እንዲሁም ለሌማት ትሩፋት ተግባራት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንሚያበረክትም አስገንዝበዋል፡፡

የአፋር ሕዝብ ከጥንት ጀምሮ ደን፣ ጫካ እና ሌሎች የተፈጥሮ ሐብቶችን የመንከባከብ ባህል እንዳለው ገልጸው በቀጣይም አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.