Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል ድርቅ ለተከሰተባቸው አካባቢዎች ከ42 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተበረከተ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ለምግብ ዋስትና ችግር ለተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚሆን ከ42 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተበርክቷል፡፡

ድጋፉ የአለም ምግብ ፕሮግራም በድርቅ ለተጎዱ የክልሉ አርብቶ አደሮች እንዲከፈል በተደረሰው ስምምነት መሰረት በኢትዮጵያ መድን ድርጅት፣ ኒያላ፣ ኦሮሚያና አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያዎች አማካኝነት ክፍያው ተፈፅሟል ነው የተባለው፡፡

የኢንሹራንሽ ክፍያው በሶማሌ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም በኩል በ10 ወረዳዎች ለሚገኙ 24 ሺህ 966 አባወራዎች እንደሚደርስ የክልሉ ግብርና ቢሮ እና የእንስሳት እና አርብቶ አደር ልማት ቢሮ ማስታወቁን ከሶማሌ ክልል ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.