Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የ”ኒው ዴቨሎፕመንት ባንክ” አባል ለመሆን እየሰራች መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የብሪክስ ባንክ በሆነው “ኒው ዴቨሎፕመንት ባንክ” አባል ለመሆን እየሰራች መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ነብዩ ተድላ÷ በመዲናዋ በቅርቡ ጉብኝት ያደረጉት የተመድ ምክትል ዋና ፀሀፊ አሚና መሃመድ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታዬ አጽቀስላሴ ጋር ተገናኝተው በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን አንስተዋል።

የፊታችን ሐምሌ ወር ኢትዮጵያ 4ኛውን ፋይናንስ ለልማት ኮንፈረንስ በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ ዝግጅት እያደረገች መሆኑን ገልጸው÷ ለዚሁ ስራ ከመንግስታቱ ድርጅትና ሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር እየተሰራ እንደሆነ ገልፀዋል።

በተመሳሳይ ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ እና ስሎቬኒያ የሁለትዮሽ ትብብር ለማጠናከር ያለመ ምክክር መደረጉን ገልፀዋል።

የሊቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር በአዲስ አበባ ያደረጉት ጉብኝት ስኬታማ እንደነበር ጠቅሰው፤ በጉብኝታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር ሀገራቱ በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን አንስተዋል።

በሩሲያ ሞስኮ ከተማ በተደረገው የብሪክስ አባል ሀገራት ምክክር በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ እንደተሳተፈ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በምክክር መድረኩ የብሪክስ አባል ሀገራት ተሳትፎ መገምገሙንና ለቀጣይ የቡድኑ ስብሰባ ግብዓት የሚሆኑ ሃሳቦች መነሳታቸውን ጠቁመዋል፡

ኢትዮጵያ የብሪክስ ባንክ በሆነው “ኒው ደቨሎፕመንት ባንክ” አባል እንድትሆን በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.