Fana: At a Speed of Life!

በቅርቡ የተሾሙት አምባሳደሮች ምደብ ቦታ ይፋ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቅርቡ በኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የተሾሙት አምባሳደሮች ምደብ ቦታ በዛሬው እለት ይፋ ተደረገ።

ኢትዮጵያን በተለያዩ አገራት የሚወክሉ 15 አዳዲሰ አምባሳደሮችን ሹመት የካቲት 24 ቀን 2012 ዓም ይፋ መደረጉ የሚታወስ ሲሆን፥ በዚሁ መሰረት አምባሳደሮቹ የሚመደቡባቸው አገራት ከዚህ በሚከተለው መሰረት ተወስኗል።

ባለሙሉ ስለጣን አምባሳደሮች፦

1. አምባሳደር ብርሁኑ ፀጋዬ አውስትራሊያ ካንቤራ

2. አምባሳደር ያለም ፀጋይ ኩባ ሃቫና

3. አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ቤልጄም ብራሰልስ

4. አምባሳደር ዶክተር ማርቆስ ተክሌ ግብጽ ካይሮ

5. አምባሳደር ባጫ ጊና ሞሮኮ ራባት

6. አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ሱዳን ካርቱም

7. አምባሳደር ምህረታብ ሙሉጌታ ኤርትራ አስመራ

8. አምባሳደር ነብያት ጌታቸው አልጀሪያ አልጀርስ እንዲሁም

9. አምባሳደር ተፈሪ መለስ እንግሊዝ ለንደን እንዲሰሩ ተመድበዋል።

እንዲሁም አምባሳደሮች

1. አምባሳደር አድጎ አምሳያ ስዊድን ስቶክሆልም ምክትል ሚሲዮን መሪ

2. አምባሳደር ጀማል በከር ባህሬን ማናማ ቆንስል ጄኔራል

3. አምባሳደር አብዱ ያሲን ሳኡዲ አረቢያ ጄዳ ቆንስል ጄኔራል

4. አምባሳደር ለገሠ ገረመው ካናዳ ኦታዋ ቆንስል ጄኔራል

5. አምባሳደር እየሩሳሌም አምደማርያም የተባበሩት አረብ ኢሚሪቶች ዱባይ ቆንስል ጄኔራል

6. አምባሳደር ሽብሩ ማሞ አሜሪካ ሚኒሶታ ቆንስል ጄኔራል እንዲሰሩ ተመድበዋል።

አምባሳደሮቹ በተመደቡባቸው ሀገራት የፕሮቶኮል አሰራር መሰረት አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተጠናቅቆ በቅርቡ
ወደ ምድብ ቦታቸው ተንቀሳቅሰው ስራቸውን በይፋ የሚጀምሩ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.