Fana: At a Speed of Life!

በበጀት ዓመቱ 49 ሚሊየን ዶላር ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሃብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ሥራ ጀምረዋል- ኮርፖሬሽኑ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተጠናቀቀው 2014 በጀት ዓመት 49 ሚሊየን ዶላር የኢንቨስትመንት መነሻ ካፒታል ያስመዘገቡ ዘጠኝ ባለሃብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ሥራ መጀመራቸውን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ገለጸ።

የኮርፖሬሽኑ የማርኬቲንግና ኮሙኒኬሸን መምሪያ ኃላፊ አቶ ሔኖክ አስራት እንደገለጹት÷ 49 ሚሊየን ዶላር የኢንቨስትመንት መነሻ ካፒታል ያስመዘገቡ ዘጠኝ አዳዲስ የአገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶች በተለያዩ ዘርፎች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ገብተው ሥራ ጀምረዋል፡፡

ባለሃብቶቹ በጨርቃጨርቅና በአቮካዶ ዘይት ማምረት ላይ መሰማራታቸውንም ጠቅሰው ኢትዮጵያ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የምታስገባቸውን ምርቶች በአገር ውስጥ ለመተካት ኢንዱስትሪ ፓርኮች በትኩረት እየሠሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በ2015 በጀት ዓመት በኢትዮጵያ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያለውን ምቹ አማራጭ በማስተዋወቅ የተሻለ ኢንቨስትመንት ለመሳብ በትኩረት ይሠራል ማለታቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመላክታል።

እስካሁን በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች 13 ኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመገንባት ከ120 በላይ ባለሃብቶች ገብተው እንዲሠሩ ማድረግ እንደተቻለና ከ85 በመቶ በላይ የሚሆኑት ግዙፍ የኢንቨስትመንት አቅም ያላቸው የውጭ አገር ባለሃብቶች መሆናቸውን አቶ ሔኖክ ተናግረዋል፡፡

በዚህም ከ83 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው ሲሆን÷ ከ85 በመቶ በላይ የሚሆኑት ወጣት ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.