Fana: At a Speed of Life!

በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ወልቂጤ ከተማ ጅማ አባጅፋርን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ29ኛ ሣምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ረፋድ ላይ በተካሄደ ጨዋታ ወልቂጤ ከተማ ጅማ አባ ጅፋርን 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡
የወልቂጤ ከተማን የአሸናፊነት ጎሎች÷ ዋህብ አዳምስ፣ በኃይሉ ተሻገር እና ጫላ ተሸታ አስቆጥረዋል፡፡
ክትፎዎቹ ማሸነፋቸውን ተከትሎ÷ ነጥባቸውን 35 በማድረስ ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር 8ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችለዋል፡፡
ጅማ አባ ጅፋር እና ሰበታ ከነማ ከቀናት በፊት ከፕሪሚየር ሊጉ መውረዳቸውን ማረጋገጣቸው ይታወሳል፡፡

 

ቀትር ላይ በተደረገ ጨዋታ ደግሞ ሃዲያ ሆሳዕና ከወላይታ ዲቻ 2 አቻ ተለያይተዋል።

ዑመድ ዑኩሪ የሃዲያን ጎሎች ሲያስቆጥር አናጋው ባደግ እና ፍሬዘር ካሳ የወላይታ ዲቻን የአቻነት ጎሎች አስቆጥረዋል።

 

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.