Fana: At a Speed of Life!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተወሰደ እርምጃ በአካባቢው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ፀረ ሰላም ሃይሎች ተደመሰሱ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ ዕዝ የ22ኛ ንስር ክፍለ ጦር ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በወሰደው ወታደራዊ እርምጃ በቀጠናው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ፀረ ሰላም ሃይሎች ተደመሰሱ ።
የ22ኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ኮሎኔል ሰይፈ ኢንጊ እንደገለፁት፥ በግብፅና ሱዳን ድጋፍ በአሸባሪው ህወሓት አዝማችነት የህዝቡን ሰላም ለማወክ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሸርቆሌና መንጌ ሰርገው የገቡ ፀረ ሰላም ሃይሎች መከላከያ ሰራዊቱና የክልሉ ፀጥታ ሃይል በቅንጅት በወሰደው እርምጃ ሊደመሰሱ ችለዋል ።
የአሸባሪው ህወሓት ጀሌዎች ታጥቀውት የነበረ 1 ሺህ 262 የክላሽ ጥይት ፣ 8 ቦንብ ፣ 8 ክላሽ ፣ 3 ፀረ ተሽከርካሪ ፈንጅ ፣ 1 መገናኛ ሬድዮ ፣ 1 አር ፒ ጂ ፣ 18 የአር ፒ ጂ ቅንቡላ ፣ 1 የአር ፒ ጂ መነፅር ተማርኳል ።
4 የብሬን ጥይት ፣ 1 የብሬን ዝናር ፣ 11 የሞርተር 82 ካምሱር ፣ 4 ወታደራዊ የወገብ ትጥቅ ፣ 5 ፀረ ሰው ፈንጅ ፣ 900 የሱዳን ፖውንድ እና 29 የክላሽ ካዝና በሰራዊቱ መማረኩን ኮሎኔል ሰይፈ ኢንጊ ገልጸዋል ።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ኮማንደር አብዱላሃዚም መሃመድ በበኩላቸው፥ ህዝቡ የጀመረውን የለውጥና የልማት ጉዞ ለማደናቀፍ የውጭ ጠላቶች ከውስጥ ጠላት ጋር ተቀናጅተው በሱዳን ድንበር በኩል ቢገቡም በፀጥታ ሃይሉና በመከላከያ ሰራዊቱ የጋራ ስራ ከ30 በላይ ፀረ ሰላም ሃይሎች ሲደመሰሱ የተቀሩትን ደግሞ ምርኮኛና ቁስለኛ በማድረግ ያሰቡት እኩይ ተግባር እንዳይሳካ ተደርጓል ብለዋል።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሰላም ግንባታና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ሙሳ መሃመድ ፣ የክልሉ ፀጥታ ሃይል ከጀግናው የአገር መከላከያ ሰራዊት ጋር የአሰሳና ቅኝት ስራዎችን በማከናወን የክልሉ ሰላም አስተማማኝ እንዲሆን ውጤታማ ስራዎችን እየፈጸመ እንደሆነ ማረጋገጣቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.