Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ለሚፈጠረው ችግርና ርሃብ ተጠያቂው አሸባሪው ህወሃት ነው- ዶክተር አረጋዊ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “በትግራይ ለሚፈጠረው ችግርና ርሃብ አሸባሪውን ህወሃት ተጠያቂ ማድረግ ሲገባ ወደ ፌዴራሉ መንግስት ማላከክ ፍፁም ተቀባይነት የለውም” ሲሉ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶክተር አረጋዊ በርሔ አስገነዘቡ።
የቀድሞ ወዳጅነትን ተገን በማድረግ ዕርዳታ ማስተጓጎልና ዲፕሎማሲያዊ ጫና ለመፍጠር መሞከር ተቀባይነት የለውም ብለዋል።
ዶክተር አረጋዊ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ አሸባሪው ቡድን ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ በስልጣን ላይ ሲቆይ ከትግራይ ባለፈ በመላ አገሪቷ ለሚኖሩ ህዝቦች ስቃይና መከራ እንደነበር አስታውሰዋል።
ቡድኑ የኢትዮጵያን ሃብቶች በስግብግብነት ከመቆጣጠርና ከመዝረፍ ባለፈ ለትግራይ ህዝብ የልማትና የፍትህ ጥያቄ ምላሽ እንዳልነበረውም ጠቅሰዋል።
በኢትዮጵያ ለተከሰተው ምስቅልቅል የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ችግሮች ሁሉ ዋነኛ ተጠያቂው ራሱ አሸባሪው ቡድን ነው ብለዋል ዶክተር አረጋዊ።
“በትግራይ ህዝብ ስም ሲነግድና ሃብት ሲሰበስብ የቆየው ይህ ቡድን፤ ከራሱ ጥቅምና ፍላጎት ውጪ የትግራይ እናቶችና ህጻናትን ስቃይ የሚሰማ ጆሮ፥ የሚያይ ዓይን የለውም” ነው ያሉት።
የአሸባሪ ቡድኑ እኩይ ድርጊት ለማንም የተደበቀ ባይሆንም፥ የውጭ ሃይሎች ድርጊቱን ከማውገዝ ይልቅ ደግፈው መቆማቸው “በትግራይ ህዝብ ላይ ማፌዝ ነው” ብለዋል።
አሸባሪው ቡድን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ይፋዊ ጦርነት መክፈቱን ተከትሎ፥ ለትግራይ ህዝብ የሚደርሰው ሰብዓዊ ድጋፍ እንዳይቋረጥ መንግስት ያለሰለሰ ጥረት ሲያደርግ እንደቆየ አንስተዋል።
ይሁንና ከትግራይ አልፎ ወደ አጎራባች ክልሎች ሰርጎ በመግባት የተለያዩ ሰብአዊና ቁሳዊ ወድመቶችን በማድረስ ላይ መሆኑን ገልፀዋል።
የሽበር ቡድኑ ድርጊት ለማንም ግልፅ ሆኖ እያለ፥ በውጭና በአገር ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ የቡድኑ ደጋፊዎች የሚሰጡት የሀሰት ምስክርነት እንዳሳዘናቸው ዶክተር አረጋዊ ተናግረዋል።
ለትግራይ ህዝብ ሰብአዊ እርዳታ ተደራሽ ለማድረግ ወደ ስፍራው የተላኩ ተሽከርካሪዎችን በማስቀረት አሸባሪው ሃይል ለጦርነትና ዝርፊያ እንዲውሉ ማድረጉንም ጠቅሰዋል።
በተለይም የአሜሪካ መንግስት አስተዳደር አካላት መካከል ከሽብር ቡድኑ አመራሮች ጋር በነበራቸው የቀድሞ ወዳጅነት በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ያልተገባ ጫና ለማድረስ እየሰሩ መሆኑንም ነው ያስረዱት።
የእነዚህ አካላት ድርጊት ኢትዮጵያና አሜሪካ ያላቸውን የረዥም ጊዜ ወዳጅነት ለማበላሸት ዓላማ ያደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ ህዝብ በመረጠው አዲስ መንግስት ላይ ያልተገባ ጫና ለመፍጠር መሞከርም ፍፁም ተቀባይነት የለውም ብለዋል ዶክተር አረጋዊ።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.