Fana: At a Speed of Life!

በአስር ዓመቱ የልማት ዕቅድ ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር ኢትዮጵያ እየተገበረችው በምትገኘው የአስር ዓመቱ የልማት ዕቅድ ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ከልማት አጋሮች ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡
በበይነ መረብ በተካሄደው በዚህ ውይይት ላይ የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)፣ የገንዘብ ሚኒስትር ዴዔታ ሰማሪታ ሰዋሰው እንዲሁም የተለያዩ የልማት አጋሮች ተወካዮች ተሳትፈዋል።
በትግበራ ላይ ባለው የአስር ዓመቱ የልማት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ዶክተር ፍጹም አሰፋ በሰጡት ማብራሪያ፥ የእቅዱ የመጀመሪያ ዓመት አፈፃፀም ላይ የኮቪድ-19 ወረረሽኝ የኢኮኖሚ ጫና ባለበትም ሁኔታ የተሻለ አፈፃፀም መታየቱን ጠቁመው፥ በወጪ ንግድ ዘርፍ፣ በሀገር ውስጥ ገቢ አሰባሰብ እና በግል ዘርፍ ልማት ላይ የላቀ ውጤት ለማስመዝብ ተችሏል ብለዋል፡፡
መንግስት አሁን ባለበት ሁኔታ ውስጥ ሆኖ የልማት ግቦቹን እና አላማውን ለማሳካት የሚያደርገውን ጥረት ለማሳካት ቁርጠኛ ነው ያሉት ሚኒስትሯ፥ መንግስት ያቀዳቸው የተለያዩ የልማት ፕሮግራሞች በትግበራ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ከዚሁ ጋር በተገናኘ በቅርቡ መንግስት እያዘጋጀ ካለው የማገገሚያ እና የመልሶ ግንባታ ፕሮግራም ዕቅድ ጋር የ10 አመት የልማት ፕሮግራሙ ተጣጥሞ የሚሄድበትን መንገድ የሚመቻች መሆኑንም ጨምረው መጠቆማቸውን ከፕላን እና ልማት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በመንግስት መሪነት የሚዘጋጀው የማገገሚያ እና የመልሶ ግንባታ ፕሮግራም እቅድ ፥ ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት በአጭር ጊዜ እንዲሁም በረዥም ጊዜ የልማት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ እንዲሁም በማገገሚያ ፕሮግራም ዕቅዱ ላይ የሚሳተፉበትን መድረክ እንደሚመቻችም ነው ያስታወቁት፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.