Fana: At a Speed of Life!

በአቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራው ልዑክ በዱግዳ ወረዳ በክላስተር የሚመረተውን የፓፓዬ ማሳ ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራው ልዑክ በዱግዳ ወረዳ በ10 ሄክታር መሬት ላይ በክላስተር የሚመረተውን የፓፓዬ ማሳ በመጎብኝት አርሶ አደሮችን አበረታቷል፡፡

እንደ ኦሮሚያ ክልል በ 1ሺህ 200 ሄክታር መሬት ላይ የፓፓዬ ምርት እየተመረተ እንደሚገኝ የክልሉ ግብርናና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ጌቱ ገመቱ ተናግረዋል፡፡

አርሶ አደሮቹ በርካታ ምርት ቢያመርቱም ያለ አግባብ ጣልቃ በሚገቡ ደላሎች ምክንያት ለጤናማ የገበያ ትስስሩ እንቅፋት እንደሆነባቸው እና ተገቢውን ጥቅም አለማግኘታቸውን ገልጸዋል፡፡

አቶ ሽመልስ አብዲሳ ÷የገበያ ትስስሩ ህጋዊ እንዲሆን የኦሮሚያ ክልል መንግስት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በመሆን ” ኦሮ ፍሬሽ” የሚባለው የገበያ ስርዓት አርሶ አደሩን እና ገበያውን የሚያገናኛ እንዲሆን እየተሰራ ነው ብለዋል ፡፡

በጀሚላ ጀማል እና አዲሱ ሙሉነህ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.