Fana: At a Speed of Life!

በአቶ አወል አርባ እና በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ራይነር የተመራ ልኡክ ኤርታሌን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ እና በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ራይነር የተመራ ልኡክ በኤርታሌ እሳተ ጎሞራ ጉብኝት አድርጓል።

ጉብኝቱ በክልሉ የሚገኙ የቱሪስት መስህቦችን ማስተዋወቅ እና በክልሉ የቱሪስቶችን ፍሰት ቁጥር ለመጨመር ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።

የልዑካን ቡድኑ በቀጣይ በክልሉ የሚገኙ ሌሎች የቱሪስት ቦታዎችን የሚጎበኝ መሆኑን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከሀገሪቱ የቱሪስት መዳረሻዎች መካከል አንዱ የሆነውና በአብዛኛው ከመስከረም እስከ መጋቢት ባሉት ወራት የሚጎበኘው ኤርታሌ፥ በአፋር ክልል ዞን ሁለት ኪልባቲ ረሱ አካባቢ ይገኛል።

የኤርታሌ እሳተ ገሞራ የበርካታ ቱሪስቶች እና ሳይንቲስቶች ቀልብ የሚስብ ድንቅ የቱሪስት ቦታ ነው።

“ኤርታሌ” የአፋረኛ ቃል ሲሆን ትርጉሙም “የሚጨስ ተራራ” ማለት ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.