Fana: At a Speed of Life!

በኢሉባቦር ዞን የመንግስት ሰራተኞች እና የምዕራብ አርሲ ዞን ነዋሪዎች ለመከላከያ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 16 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢሉባቦር ዞን የመንግስት ሰራተኞች የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለአገር መከላከያ ሰራዊት የ50 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ።

የምዕራብ አርሲ ዞንም ለ3ኛ ዙር 211 ሰንጋ በሬዎችን ለመከላከያ ድጋፍ አድርገዋል።

የወር ደመወዛቸውን ድጋፍ ያደረጉት ሰራተኞቹ እንዳሉት በአሸባሪው ህወሓት የተደቀነው ወቅታዊ የሕልውና አደጋ በኢትዮጵያውያን የተባበረ ክንድ ባጭር ጊዜ እንዲቀለበስ ድጋፋችን ቀጣይ ነው።

ሰራተኞቹ የአገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር የሕይወት መስዕዋትነት ጭምር እየከፈለ ላለው ሠራዊት ያደረጉት ድጋፍ በጣም ትንሹን መሆኑን ተናግረዋል።

ሕይወቱን እየሰጠ ላለው ሠራዊት ያደረጉት ድጋፍ እየከፈለ ካለው መስዕዋትነት ጋር የማይነፃፀር መሆኑንም አስረድተዋል።

ከአገር ሕልውና የሚቀድምና የሚሰሰሰት ነገር ከቶውንም ስለማይኖር ድጋፋቸውን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ነው የተናገሩት።

በብልፅግና ፓርቲ የዞኑ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ እንዳለ ደምሴ እንዳሉት የዞኑ የመንግሥት ሰራተኞች እስካሁን ለአገር መከላከያ ሠራዊት 50 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል።

በተመሳሳይ የምዕራብ አርሲ ዞን ነዋሪዎች ለሕልውና ዘመቻው ስኬት ለሦስተኛ ጊዜ 211 ስንጋ በሬዎችን ለመከላከያ ስራዊት ድጋፍ አድርገዋል።

የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አህመድ ሃጅ የዞኑ ሕዝብ አሸባሪው ህወሓት ጦርነት ከከፈተበት ጊዜ ጀምሮ ለሕልውና ዘመቻው ስኬት እያደረገ ያለውን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠሉን ኢዜአ ዘግቧል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.