Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር አካባቢ ግጭት እንዲፈጠር ድብቅ አፍራሽ አጀንዳ ይዘው የሚንቀሳቀሱ አካላት ተንኮል ነው – የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር አካባቢ ግጭት እንዲፈጠር የሚደረገው ጥረት ድብቅ አፍራሽ አጀንዳ ይዘው የሚንቀሳቀሱ አካላት ተንኮል መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በዓረብኛ ባወጣው መግለጫ የሁለቱ ሀገራት ወሰን ላይ የተከሰተው ችግር ሀገራት የማይወክል እና የማይመጥን ነው ብሏል፡፡

ጉዳዩ የሁለቱ ሀገራት መንግስትና ህዝብ ፍላጎትም አይደለምም ነው ያለው፡፡

ፅህፈት ቤቱ በመግለጫው በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ያለው የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ታሪካዊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በሴረኞች ፍላጎት ሊቀለበስ እንደማይችልም ጠቅሷል፡፡

የሁለቱ ሀገራት ህዝቦች የጋራ ማንነት ያላቸው ጠንካራ ህዝቦች መሆናቸውንም ፅህፈት ቤቱ አስታውቋል፡፡

የሰሞኑ ሁነት ጥርጣሬ እና ግጭት ለመፍጠር እና ሁለቱን ሀገራት ሰላም ለመንሳት የተሸረበ ሴራ ነው ሲልም አብራርቷል፡፡

ሁለቱ ሀገራት ካላቸው ታሪካዊ ግንኙነት አንፃር ችግሩን በመነጋገር ለመፍታ የኢትዮጵያ መንግስት እንደሚሰራ ገልፆ፣ የተፈጠረው የፀጥታ ችግር ለሁለቱ ሀገራት የሚበጅ አለመሆኑን አስረድቷል፡፡

ኢትዮጵያ በሰሜን የሃገሪቱ ክፍል የህግ ማስከበር ስራን አጠናቃ የመልሶ ግንባታና ሰብዓዊ ድጋፍ ማቅረብ ላይ ባለችበት ሱዳንም ከህዝባዊ ተቃውሞ መልስ ባለችበት ጊዜ ችግሩ መከሰቱ አሳዛኝ ያደርገዋልም ብሏል ፅህፈት ቤቱ፡፡

በሁለቱ ሀገራት እና ሕዝቦች መካከል ያለውን ወንድማቻዊ ግንኙነት በማይመጥን መልኩ በሴራ ግጭት ለመፍጠር የሚሰራውን ስራ መንግስት እየተከታተለው መሆኑን አውስቷል፡፡

የሱዳን መንግስትም ቢሆን ችግሩን የማይደግፈው ድርጊት መሆኑን በመግለጫ አስታውቋል ነው ያለው፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.