Fana: At a Speed of Life!

በኩዌት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኩዌት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵውያን ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ የሚውል ገንዘብ በማሰባሰብ በኩዌት የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስረከቡ፡፡
240 ሺህ ብር በማሰባሰብ ለዚህ ተግባር ወደ ተከፈተው የባንክ አካውንት ገቢ በማድረግ ደረሰኙን በኩዌት የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስረክበዋል ተብሏል፡፡
ከዚህ ቀደም ለኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እንዲሁም በተለያዩ ጊዜያት ለሚቀርብላቸው ሀገራዊ ጥሪ ምላሽ በመስጠት ከሀገራቸው ጎን መቆማቸውን ሲያረጋግጡ ቆይተዋል መባሉን ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.