Fana: At a Speed of Life!

በኮሮናቫይረስ የመያዝ ምጣኔ በኢትዮጵያ የ12 ነጥብ 8 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል – የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 2 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኮሮናቫይረስ የመያዝ ምጣኔ በኢትዮጵያ የ12 ነጥብ 8 በመቶ ጭማሪ  ማሳየቱን የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገለጸ።

ይህ በኮሮናቫይረስ የመያዝ ምጣኔ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ  2 በመቶ፣ በአፍሪካ 10 በመቶ መጨመሩንም  ነው የገለጸው።

ኢንስቲትዩቱ በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ስርጭት አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ እየጨመረ ነው  ሲልም  አስጠንቅቋል።

ባሳለፍነው ሳምንትም ከየካቲት 22 እስከ 28 ቀን 2013  ዓ.ም በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር የ2 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

በአፍሪካም በዚሁ ሳምንት በቫይረሱ የመያዝ ምጣኔ በ10 በመቶ የጨመረ ሲሆን በተለይ በኢትዮጵያ ደግሞ ከዚህም አልፎ በ12 ነጥብ 8 በመቶ አድጓል፡፡

በትናንትናው ዕለት የኮቪድ-19 የላቦራቶሪ ምርመራ ካደረጉ 7 ሺህ 819 ሰዎች መካከል 1 ሺህ 543ቱ የኮቪድ-19 ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡

ይህ ማለት ከተመረመሩት 100 ግለሰቦች 20 ያህሉ ወይም 20 በመቶ ኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ከፍተኛ ቁጥር የተመዘገበው በነሐሴ ወር 2012 ዓ.ም  ማህበረሰብ አቀፍ ንቅናቄና የምርመራ ዘመቻ በተካሄደበት ወቅት ነው፡፡

በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ ያለው የፅኑ ሕሙማን ቁጥርም ትናንት 438 ደርሷል፡፡

ይህ ቁጥር ኮቪድ-19 ወደ አገሪቱ ከገባ ጀምሮ ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

በትናንትናው እለት ብቻ 15 ግለሰቦች በኮቪድ-19 ምክንያት ሕይወታቸውን ያጡ ሲሆን የሟቾች አጠቃላይ ቁጥር 2 ሺህ 446 ደርሷል፡፡

የቫይረሱ ስርጭት በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች በፍጥነት እና በአስደንጋጭ ሁኔታ እየተዛመተ መሆኑን  ገልጸዋል።

ኢንስቲትዩቱ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ማስክ በመልበስ እንዲሁም አካላዊ ርቀታቸውን እና የእጃቸውን ንጽህና በመጠበቅ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የሚያደርሰውን ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት በጋራ እንዲከላከሉ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.