Fana: At a Speed of Life!

በወ/ሮ ዳግማዊት የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት ልዑክ ቡድን ፖርት ሱዳንን ጎበኘ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 22 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የሚመራው የልዑካን ቡድን ፖርት ሱዳንን ጎበኘ፡፡

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በተሳተፉበት በዚህ ጉብኝት የሱዳን መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ሚኒስትር ዲኤታ ኦማር አህመድ ሞመሀድ እና የሱዳን ባህር ወደብ ኮርፖሬሽን ዳይሬክተር ጄኔራል ኦኖር ሙሳ ተገኝተዋል፡፡

በዚህ ወቅም የስራ ሃላፊዎች በወደብ አገልግሎትና አጠቃቀም ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡

ይህንን ተከትሎ የሱዳን ባህር ወደብ ኮርፖሬሽን ኢትዮጵያ ለገቢና ወጪ ንግድ ዕቃዎች የሱዳንን ወደብ ስትጠቀም አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርግ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

እንዲሁም በቅርቡ ለሚጀመረው ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ የማስገባት ሂደትን እንዲያግዝ የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርና ሎጅስቲክ አገልግሎት ድርጅት ማስተባበሪያ ቢሮ በኮርፖሬሽኑ በኩል ለማዘጋጀት ተስማምተዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም የወደቡን አጠቃቀም ለማሳለጥና ቴክኒካል ጉዳችን የሚሰራ ኮሚቴ ለማቋቋም ከስምምነት የደረሱ ሲሆን፥ ኮሚቴውም በ15 ቀናት ውስጥ የመጀመሪያ ስብሰባውን እንደሚያካሂድ ተነግሯል፡፡

በፈረንጆቹ 2003 የሱዳን መንግስት ለኢትዮጵያ ሎጅስቲክ አገልግሎት እንዲውል 875 ሺህ ካሬ ሜትር በፖርቱ አቅራቢያ መስጠቱ ይታወሳል።

ይሁን እንጅ እስካሁን ድረስ በአግባቡ ርክክብ ተደርጎ አገልግሎት ላይ ያልዋለ በመሆኑ አስፈላጊውን ሁኔታ በማቻቸት ቦታውን በሥራ ላይ ለማዋል ከስምምነት መደረሱን ከሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.