Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ወሎ ዞን ለአሸባሪው ሸኔ ሊተላለፍ የነበረ ከ3 ሺህ 600 በላይ ሕገ ወጥ ጥይት ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ወሎ ዞን ወግዲ ወረዳ ለአሸባሪው ሸኔ ሊተላለፍ የነበረ 3 ሺህ 664 ሕገ ወጥ ጥይት ተያዘ፡፡
ግንቦት 12 ቀን 2014 ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ላይ መነሻውን ቦረና ወረዳ አድርጎ ወግዲ አቋርጦ ደራ ለኦነግ ሸኔ ሊተላለፍ የነበረ የክላሽ ጥይት በወግዲ ወረዳ 06 ቀበሌ በወረዳው የጸጥታ አካላት ተይዞ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን የወረዳው ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ኮማንደር ንጋቱ ታመነ እንደገለጹት፥ በየደረጃው የሚገኘው የጸጥታ መዋቅር ሕገ ወጥነትን ለማስተካከል በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
በዛሬው ዕለት በሕገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር ለተያዘው ጥይት ህብረተሰቡ ላደረገው ጥቆማ ምስጋና ማቅረባቸውን ከወረዳው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.