Fana: At a Speed of Life!

በድሬዳዋ የኢንዱስትሪ ኮምፕሌክስ ሊገነባ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)  በኢስት አፍሪካ ሆልዲንግ እና በቻይናው ዌስት ኢንተርናሽናል ሆልዲንግ የሚገነባው የድሬዳዋ ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ ኢንደስትሪያል ኮምፕሌክስ የብረታ ብረት ፋብሪካ በድሬደዋ ከተማ ለመገንባት የሚያስችል የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ።

የመሠረት ድንጋዩን ያኖሩት የኢፌዴሪ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ  አቶ አደም ፋራህ ናቸው።

ፋብሪካው የሚገነባው በ103 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ሲሆን÷ የሲሚንቶ ፋብሪካው በቀን 5 ሺህ ቶን ሲሚንቶ የማምረት አቅም አለው ተብሏል።

የብረታ ብረት ፋብሪካው በአመት 700 ሺህ ቶን የሚያመርት ሲሆን ለ 10 ሺህ ሰዎች የስራ ዕድል እንደሚፈጥር ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.