በዶዶላ ከተማ ከ8 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ ህገ ወጥ ተንቀሳቃሽ ስልኮች ተያዙ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን በዶዶላ ከተማ ከ8 ሚሊየን 200 ሺህ ብር በላይ የሚያወጡ 2 ሺህ 998 ህገ ወጥ ተንቀሳቃሽ ስልኮች ተያዙ።
ተንቀሳቃሽ ስልኮቹ ከባሌ ዞን ሮቤ ከተማ ወደ ሻሸመኔ በተሽከርካሪ ተጭነው ሲጓዙ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን የዶዶላ ከተማ ፖሊስ ፅህፈት ቤት ዋና ኢንስፔክተር መሀመድ ዎቲቻ ተናግረዋል።
ተንቀሳቃሽ ስልኮቹን ጭኖ ሲጓዝ የነበረው ተሽከርካሪ ሹፌር በቁጥጥር ስር ውሎ ማጣራት እየተካሄደበት መሆኑንም ገልፀዋል።
በጌታቸው ሙለታ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!