Fana: At a Speed of Life!

በግብርና ምርት ያለውን አቅም ለመጠቀም የቅዝቃዜ ሰንሰለቱን የጠበቀ ምርት ማቅረብ ይገባል ተባለ

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በግብርና ምርት ያላትን እምቅ አቅም ጥቅም ላይ ለማዋል የቅዝቃዜ ሰንሰለቱን የጠበቀ ምርት ለገበያ ማቅረብ ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ።

በተለይም አቮካዶን በፍጥነት ለሚፈለገው ገበያ ማቅረብ የምርት ብክነትን ከማስቀረቱም በላይ የኢትዮጵያን ምርት ተመራጭ ያደርገዋል ተብሏል።

የኢትዮጵያ እና የኔዘርላንድስ መንግስት ለሁለት አመት ሲያደርጉት የነበረው የአቮካዶ የምርት ሰንሰለት ጥናት ዛሬ ይፋ ሆኗል።
ይህም ምርቱ ቅዝቃዜውን ጠብቆ ለአገርም ውስጥም ይሁን ለዓለም አቀፉ ገበያ ለማቅረብ የሚያስችል ፕሮጀክት ነው ተብሏል።

በተለይም አሁን ላይ ሰፊ የሆነ የዓለም አቀፍ ገበያ መኖሩን ጥናቱን ከኔዘርላንድስ በበይነ መረብ ያቀረቡት ስቴቨን ቲስራኮስ ገልጸዋል።

አሁን ላይም የአቮካዶ ምርትን ለገበያ ለማቅረብ ከፍተኛ የገበያ ፍላጎት ያለባቸው አገራት እና አካባቢዎች ተለይተዋል።

በዚህም ብሪታኒያ፣ የመካከለኛው ምስራቅ አካባቢ ለኢትዮጵያ ባለው ቅርበትና የቀጠናው አገራት በግብርና አምራችነት የማይታወቁ በመሆኑ፣ ቻይና እና ሩሲያ በምጣኔ ሃብታዊ ጥንካሬያቸው እና ባላቸው የህዝብ ብዛት መነሻ በጥናቱ ምቹ የገበያ መዳረሻ ተደርገው ተጠቅሰዋል።

ጥናቱ በተለይም የአቮካዶ ምርት የቅዝቃዜ ሰንሰለቱን ጠብቆ ለገበያ እንዲቀርብ የሚያስችሉ የኮንቴነሮችን፣ መጋዘኖችን ግንባታ የሚጠይቅና በተጨማሪም በትራንስፖርት ላይም ይህንን ማሟላት የሚጠይቅ ነው።

ለፕሮጀክቱ በሶስት ዙር በሚመደብ ከ50 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ያስፈልጋል ተብሏል።

ለጥናቱ ውጤታማነትም ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን በመወጣት የቅዝቃዜ ሰንሰለቱን በተግባር ለማዋል መስራት እንደሚጠበቅባቸውም ተነስቷል።

ጥናቱን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር እየመራው የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን፣ የግብርና ሚኒስቴር፣ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈውበታል።

ቀዝቃዛ የገበያ ሰንሰለት አንድ ምርት ከተመረተ በኋላ ለገበያ በሚቀርብብት ጊዜ ከገበሬው እስከ ተጠቃሚው እስከሚደርስ ድረስ በቀዝቃዛ መጓጓዣዎች፣ ኮንቴነር፣ የባቡር ትራንስፖርት ለገበያ የማቅረብ ሂደት ነው።

በምስክር ስናፍቅ

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.