Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሲሸነፍ ፋሲል እና መቐለ ነጥብ ጥለዋል

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 4 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የ17ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ዛሬ በተለያዩ ከተሞች ተካሄደዋል።

መቐለ ላይ ባህር ዳር ከተማን ያስተናገደው መቐለ 70 እንደርታ ጨዋታውን ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት አጠናቋል።

ድሬዳዋ ከተማ ከፋሲል ከነማ፣ ወላይታ ዲቻ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ያደረጉት ጨዋታም ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

ጅማ አባ ጅፋር ከኢትዮጵያ ቡና እንዲሁም ሃዋሳ ከተማ ከሃዲያ ሆሳዕና ያደረጉትን ጨዋታም ሳይሸናነፉ አንድ አቻ በሆነ ውጤት አጠናቀዋል።

ሲዳማ ቡናን ያስተናገደው ስሑል ሽረ ደግሞ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ጨዋታውን አሸንፏል።

ሰበታ ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያደረጉት ጨዋታ ደግሞ በሰበታ ከተማ አሸናፊነት ተጠናቋል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.