Fana: At a Speed of Life!

በ2013 ዓ.ም የብልጽግና መሰረትን የመጣል ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል – የብልጽግና ፓርቲ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በ2013 ዓ.ም በኢትዮጵያ የብልጽግና መሰረትን የመጣል ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የብልጽግና ፓርቲ አስታወቀ፡፡

የፓርቲው የጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ብናልፍ አንዱአለም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት፥ 1 ቀን ብቻ በቀረው 2012 ዓ.ም የሀገሪቱን ህልውና የተፈታተኑ ችግሮችን መሻገር ተችሏል።
ለውጡን ለማደናቀፍ እና በሀገር ህልውና ጭምር የመጣ የጥፋት እንቅስቃሴ ሀገሪቱን ዋጋ አስከፍሎ አልፏል።

እንዲሁም በህዝቦች መካካል ግጭትን በመፍጠር መንግስት ያልተረጋጋ ዓመትን እንዲያሳልፍ ቢወጠንም በተለይ የኢኮኖሚ ስብራትን የመጠገን በጅምር የቀሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን የማጠናቀቅ ስኬት ተመዝግቧል ብለዋል የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ።

በዚህም በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሰርዓትን ማስፈን እና ብልጽግናን የማረጋገጥ ጥያቄን መልስ የመስጠት መሰረታዊ ተልእኮን ፓርቲው አስቀምጧል።

ፓርቲው በሀገሪቱ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት እየሰራ ነው ያሉት አቶ ብናልፍ፥ በዚህም የድርድር አማራጭን በመከተል በመግባባት ሁሉን አሳታፊ ዴሞክራሲን ለመገንባት ስራዎች ቀጥለዋል።

ፓርቲው ሰላም፣ ልማትንና ዴሞክራሲን በቀጣይ የማስፈን ሰፊ የስራ እድል የመፍጠር የኑሮ ውድነትን መፍትሄ የማሰቀመጥ ሃላፊነቶች ይጠብቁታልም ነው ያሉት ።

በ2013 የፓርቲው እቅድ በሀገሪቱ ምርጫ የሚካሄድበት ሁኔታ ከተመቻቸ በትክክለኛ መንገድ ቅቡልነት ያለው መንግስት የመመስረት ሂደት ይጠበቃልም ያሉት ኃላፊው፥ ፓርቲው ፍትሃዊ ፤ ዲሞክራሲያዊ በሆነ ምርጫ በማሸነፍ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ይሰራል ብለዋል።

የታላቁ የህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ የውሃ ሙሌትን በስኬት እንዲከናወን በተጠናቀቀው ዓመት እንደመሰራቱ፤ የቀጣዩ ዓመት ተግባርም ይህንኑ ፕሮጀክት ቀጣዩን ስራ ማስፈጸም ላይ ይተኮራል ነው ያሉት ።

በሀገሪቱ በተለያዩ ቦታዎች የተጀመሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን የማጠናቀቅ እና አዳዲስ የመጀመር ሂደትም እንደሚቀጥል ኃላፊው ተናግረዋል።

በመጨረሻም የፓርቲው የጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ብናልፍ አንዱአለም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ መልካም ምኞታቸውን የገለጹ ሲሆን፥ የሀገሪቱን ብልጽግና ለማረጋገጥ እያደረገ ያለውን ጥረት በአዲሱ አመትም አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

በሀይለየሱስ መኮንን

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.