Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 9 ወራት ከወጪ ንግድ 2 ነጥብ 95 ቢሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 21 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ከወጪ ንግድ 2 ነጥብ 95 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ገቢው የእቅዱን 87 ነጥብ 6 በመቶ የ ሲሆን ከ2013 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ20 ነጥብ 33 በመቶ ብልጫ ማሳየቱን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ውስጥ ግብርና 69 በመቶ፣ ኢንዱስትሪ 16 በመቶ፣ ማዕድን 15 በመቶ ድርሻ መያዛቸውንም ነው የተናገሩት።
የግብርና ዘርፉ ገቢ ከፍተኛውን ድርሻ መያዙ÷የምርቶች ስብጥር ላይ ጠንካራ ስራ መሰራት እንዳለበት አመላካች እንደሆነ ተመላክቷል፡፡
በዘርፉ ያለውን ዕድል በመጠቀም የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ የምርት አቅርቦትና የገበያ መሰረተ ልማት ጥራትን ማሻሻል፣ እየታዩ ያሉ የጸጥታ ችግሮችን በዘላቂነት መፍታት፣ የዘርፉን የኮንትሮባንድና የሕገ ወጥ የንግድ አሰራር ችግሮችን መፍታት እንደሚያስፈልግም ሚኒስትሩ አሳስበዋል፡፡
የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማሻሻልና የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በማይናጋ መሰረት ላይ ለመጣል በትጋትና በቁርጠኝነት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ መገለጹን ከንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.