Fana: At a Speed of Life!

ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፕሮግራሞቻቸውን በሰላማዊ መንገድ ማቅረብ ይችላሉ – አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከለውጡ ወዲህ በፍትህ ተቋማት፣በዴሞክራሲ ግንባታና በሰብአዊ መብት አያያዝ ላይ ጥሩ ስራዎች ቢሰሩም መሻሻል ያለባቸው ስራዎች እንዳሉ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሀመድ ተናገሩ።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ እንደገለፁት ክልሉ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዘርፍ የሰራው ስራ መስተጋብሩን የጠበቀ፥ ጤናማና ህዝብንና መንግስትን በተሻለ መንገድ ያቀራረበ መሆኑን ገልፀዋል ።

የክልሉ የለውጥ አመራር በሐሳብ ብዝሐነትና ልዕልና የሚያምን እንዲሁም የዜጎችን የመናገር ነፃነት የሚያከብር ስለመሆኑ ማሳያ ጅምሮች አሉ ብለዋል።

ህዝብ የተሰማውን በሰለጠነ መንገድ መንግስትን የመጠየቅ የዲሞክራሲ ባህልን ማዳበር እንደሚገባው ገልፀው የክልሉ መንግስትም የህዝብን ጥያቄ ለመመለስ ተግቶ እንደሚሰራ አስረድተዋል ።

አቶ ሙስጠፌ ከክልሉ ቴሌቪዥን ጋር በነበራቸው ቆይታ ስለ ምርጫንና ስለ ተፎካካሪ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ ሲገልፁ ካለፉት አመታት የተሻለ የፖለቲካ ምህዳር መኖሩን ጠቅሰዋል።

ሁሉም ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሉን የሚሉትን ሐሳብ እና ፕሮግራሞች በሰላማዊ መንገድ ፣ የህዝብና የሐገርን ሰላም በማያውክ መንገድ ማቅረብ ይችላሉ ብለዋል ።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.