Fana: At a Speed of Life!

ቶምፕሰን-ሄራ እና ዋርሆልም የአመቱ ምርጥ አትሌቶች ተብለው ተመረጡ

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሊምፒክ አሸናፊዋ ጃማይካዊቷ ኢሌን ቶምፕሰን ሄራ እና ኖርዌያዊቷ ካርስተን ዋርሆልም በ2021 የዓለም አትሌቲክስ ሽልማት የአመቱ ምርጥ አትሌቶች ተብለው ተመርጠዋል።

ቶምፕሰን-ሄራ በአመቱ በታሪክ ከተመዘገቡ ውጤቶች ከፍተኛውን ነጥብ በማስመዝገብ በቶኪዮ ኦሊምፒክ የ100 ሜትር እና 200 ሜትር አሸናፊነቷን አስጠብቃ በ400 ሜትር የዱላ ቅብብል የሩጫ ውድድር ሶስተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝታለች፡፡

“የግሌን ጥረት በማድረጌ ከቀን ወደ ቀን እያሻሻልኩ መጥቻለሁ÷ የዓለም ክብረ ወሰን ለመስበርም ተቃርቤ ነበር ስለሆነም በቅርቡ አሳካዋለሁ ብየ አስባለሁ፤ ሁሉም ነገር ይቻላል” ስትል ተደምጣለች አትሌቷ።

በቀጣይ በኦሪገን በሚካሄደው የኦሊምፒክ ውድድር ሻምፒየን መሆን ህልሜ ነው ስትልም አትሌቷ አክላለች፡፡

ዋርሆልም በበኩሉ በቶኪዮ ኦሊምፒክ በ400 ሜትር መሰናክል ወርቅ በማግኘት በአትሌቲክስ ታሪክ አስደናቂ ታሪክ አስመዝግቧል።

በኦስሎ በ46 ነጥብ 70 የዓለም ክብረ ወሰን በመስበር መሪነቱን የያዘው ዋርሆልም በጃፓን ዋና ከተማ በ45 ሰከንድ ከ94 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ክብረወሰን በመስበር ወርቅ አግኝቷል፡፡

የዓለም አትሌቲክስ ፕሬዚዳንት ሴባስቲያን ኮህ በዚህ አመት ላሳዩት አስደናቂ ስኬት የዛሬ ምሽቱን አሸናፊ እና የፍፃሜ እጩዎችን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

ዘገባው የሲ ጂ ቲ ኤን አፍሪካ ነው፡፡

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.