Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት በኤም ኤስ ኤ ቢዝነስ ግሩፕ ላይ 900 ሚሊየን ብር የሚገመት ውድምት አድርሷል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት የቅባት እህሎችና የጥራጥሬ ምርቶችን ወደ ውጭ በመላክ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በሚያስገኘው ኤም ኤስ ኤ ቢዝነስ ግሩፕ ላይ 900 ሚሊየን ብር የሚገመት ውድመት ማድረሱ ተገለጸ፡፡
 
የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚው አቶ ታምራት ሞላ ለፋና ብሮድካስቲንግ ከርፖሬት እንደገለጹት÷የአሸባሪው ህወሓት ቡድን ኮምቦልቻ ከተማን በወረራ ይዞ በቆየበት ጊዜ በከተማዋ በሚገኙ ሁለት የኤም ኤስ ኤ ቢዝነስ ግሩፕ ፋብሪካዎች ላይ ከፍተኛ ውድመት አድርሷል፡፡
 
በዚህም የሽብር ቡድኑ አባላት 900 ሚሊየን ብር በሚገመት የድርጅቱ ንብረት ላይ ውድምት ማድረሳቸውን ነው የገለጹት፡፡
 
የድርጅቱ ንብረት የሆኑ 8 ከባድ ተሽከርካሪዎች በቡድኑ ተዘርፈው መወሰዳቸውን የገለጹት ዋና ስራ አስፈጻሚው÷ የሁለቱም ፋብሪካዎች ማምረቻዎችና የቢሮ ቁሳቁስ በአብዛኛው መውደማቸውንም ጠቁመዋል፡፡
 
ኤም ኤስ ኤ ኤክስፖርት እና አማር ፒፒ የተሰኙ ሁለቱ ትልልቅ ፋብሪካዎች በሺህዎች ለሚቆጠሩ የህብረተሰብ ክፍሎች የስራ ዕድል መፍጠራቸውንም አንስተዋል፡፡
 
በብስራት መንግስቱ
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.