Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ሕወሓት የምርኮኞች ምስል በማለት በመገናኛ ብዙሃን ያሰራጨው ቪዲዮ ሀሰተኛ ነው-የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ ገጽ

አበባ፣ ህዳር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)አሸባሪው ሕወሓት የምርኮኞች ምስል በማለት በመገናኛ ብዙሃን ያሰራጨው ቪዲዮ አላማው በሃሰተኛ የተቀነባበረ ምስል ዜጎችን የማደናገር ሙከራ ነው ሲል የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ ገጽ ገለጸ፡፡
 
አሸባሪው ሕወሓት የራሱን ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ልብስ አልብሶ፣ በተጨማሪም በወረራ ከአማራና ከአፋር ክልል የወሰዳቸውን ወጣቶችና ከጦር ተመላሾች በአልመዳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ አምርቶ ተንቤን የደበቃቸውን የደንብ ልብሶች ካለበሰ በኋላ ጥቂቱን የሰው ብዛት በፊልም ኤዲቲንግ በማባዛት ለዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን ግብአትነት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
 
የምርኮኞች ምስል ተብሎ በመገናኛ ብዙሃን የተሰራጨው ቪዲዮ አላማው በሃሰተኛ የተቀነባበረ ምስል ዜጎችን የማደናገር ሙከራ ነው ብሏል የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ ገጽ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው ማብራሪያ፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.