Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው የህወኃት ጁንታ ህፃናትን እየማገደ ይገኛል

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወኃት ጁንታ ህፃናትን እየማገደ እንደሚገኝ ከአፋር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አሸባሪው ህወሃት በአፋር ጥቃት ለመሰንዘር ካሰማራቸው ሃይሎች መካከል ህጻናት እንደሚገኙበት የኮሙዩኒኬሽኑ መረጃ ይጠቁማል፡፡

ቡድኑ እስትንፋሱን ለማራዘም ህጻናትን ከእስክርቢቶ ይልቅ መሳሪያዎችን እያስታጠቀ ለአላማው እየተጠቀመባቸው ይገኛልም ነው ያለው፡፡

በዚህም ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች የአሸባሪውን ህወሃት ግፍ በመቃወም በተለያዩ ጊዜያት ድምጻቸውን እያሰሙ ነው ብሏል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.