Fana: At a Speed of Life!

አቶ ብናልፍ አንዱአለም ከደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ጋር የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል ሰበሰቡ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚንስትሩ አቶ ብናልፍ አንዱአለም ከደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ሠራተኞች ጋር በጋራ የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል ሰብስበዋል፡፡
አቶ ብናልፍ በዩኒቨርሲቲው መምህራን እና ሠራተኞች የተቀናጀ ሥራ መደነቃቸውን ገልጸው÷ ይህ ትብብር በሌሎች ሀገራዊ ጥሪዎች ተጠናክሮ እንዲቀጥልም አሳስበዋል።
የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ክንዴ ገበየሁ እንደገለጹት÷ ለሁለት ሳምንት በተካሄደው የዘማች ቤተሰብ ሰብል የመሰብሰብ ዘመቻ መምህራን እና ሠራተኞች ስኬታማ ሥራዎችን ተሠርተዋል፡፡
በሊቦ-ከምከም፣ ፎገራ፣ ደራ እና ጉና በጌምድር ወረዳዎች 142 ሔክታር የሩዝ፣ የዳጉሳ እና የባቄላ ሰብሎች ለክተት ጥሪ ዘማች ቤተሰብ፣ ለአቅመ-ደካሞች እና በመስኖ ገብ ቀጣናዎች መሰብሰብ ተችሏል ማለታቸውን ከዩኒቨርሲቲው የፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የደቡብ ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ አዲስ ተፈራ በበኩላቸው÷ የዩኒቨርሲቲው መምህራን እና ሠራተኞች በዘመቻው አመርቂና ታሪካዊ ዐሻራውን እንዳሳረፉ ተናግረዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.