Fana: At a Speed of Life!

አቶ ተመስገን ጥሩነህ የጣና በለስ ስኳር ፕሮጀክትን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 18 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች የጣና በለስ ስኳር ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል።

የጣና በለስ ስኳር ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ አቶ አንተነህ አሰጌ እንዳሉት በፕሮጀክቱ 203 ቻይናውያንና 306 የሐገር ውስጥ ባለሙያዎች እየሰሩ ነው።

በብረታ ብረታና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን የግንባታ አፈጻጸም ችግር ምክንያት ተጓቶ የነበረውን ፕሮጀክት ለማስተካከልና የግንባታ ሒደቱን ለማፋጠን በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የፕሮጀክቱ ወቅታዊ አፈጻጸም 82 በመቶ መድረሱን የተናገሩት ስራ አስኪያጁ ለቻይናውያን ተቋራጮች በወቅቱ ክፍያ እንዲፈጸምላቸውም ጠይቀዋል።

ፕሮጀክቱ በመጭው ታህሳስ ወር አጋማሽ የሙከራ ምርት እንዲጀምር እየተሰራ መሆኑን በመጥቀስም ይህ እንዲሳካ የክፍያ መዘግየቱ በአስቸኳይ መፈታት አለበት ብለዋል።

የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በበኩላቸው የፕሮጀክቱ ወቅታዊ አፈጻጸም የተሻለ መሆኑን መመልከታቸውን ነው የተናገሩት።

ፕሮጀክቱ በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅና ለቻይናውያን ባለሙያዎች የሚከፈለው ክፍያ እንዲፋጠንም ከሚመለከታቸው የፌደራል ተቋማት ጋር ተነጋግረን መፍትሔ እናስቀምጣለን ማለታቸውን አብመድ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.