Fana: At a Speed of Life!

አቶ አገኘሁ ተሻገር ከቀድሞው የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አቶ አደም ፋራህ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር ከቀድሞው የምክር ቤቱ አፈ-ጉባዔ አቶ አደም ፋራህ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸው በምክር ቤቱ ሲከናወኑ በቆዩ ጉዳዮችና በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ መክረዋል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት በቀጣይ በግጭት አፈታትና የህዝቦችን መቀራረብ በሚያጎለብቱ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ በውይይቱ ተገልጿል።

እንዲሁም በዉይይቱ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ዛራ ሁሙድና የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ዕፅገነት መንግሥቱ መገኘታቸውን ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.