Fana: At a Speed of Life!

አቶ እርስቱ ከሃይማኖት አባቶችና ሃገር ሽማግሌዎች ጋር እየተወያዩ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በክልሉ ከተለያዩ ዞኖች ከተውጣጡ የሃይማኖት አባቶች እና ሃገር ሽማግሌዎች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሆሳዕና ከተማ እየተወያዩ ነው።
 
በውይይት መድረኩ ላይ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋጤ ስርሞሎና በደቡብ ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካና ርዕዮተ አለም ዘርፍ ሃላፊ አቶ ስንታየሁ ወልደሚካኤልም ተገኝተዋል።
 
የክልሉ አመራሮች ከሀይማኖት አባቶችና ከሀገር ሽማግሌዎቹ ጋር በወቅታዊ ክልላዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር በማድረግ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.