Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ ሩስያ ለወሰደችው መርህን መሰረት ያደረገ አቋም ምስጋና አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢቨግኒ ታሪኪንን ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱም አቶ ደመቀ ቀደም ሲል ከሩስያ አቻቸው ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር ስኬታማ ውይይት ማድረጋቸውን በማስታወስ በቅርቡም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታ ጥበቃው ምክርቤት ሰብሰባ ላይ ሩስያ  ለወሰደችው መርህን መሰረት ያደረገ አቋም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ሚኒስተሩ በትግራይ ክልል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ ለአምባሳደሩ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በመንግስት በኩል የሰብኣዊ እርዳታ አቅራቢ ድርጅቶችና የሚዲያ ተቋማት በክልሉ ተገኝተው ስራቸውን እንዲያከናውኑ ምቹ ሁኔታዎች የተፈጠሩ መሆኑን ገልፀው የሚነሱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችንም ለማጣራት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል።

ነገር ግን አሁንም በመሬት ላይ ያለውን ተጨባጭ እውነታ ያላገናዘቡ ወቀሳዎች መቀጠላቸውን አስረድተዋዋል።

በቅርቡ በተካሄደው የአፍሪካ ሕብረት የሰላምና ጸጥታው ምክር ቤት ሰብሰባ ላይ  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በትግራይ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ማብራሪያ መስጠታቸውን ለአምባሳደሩ ገልጸዋል።

በዚህም በትግራይ ክልል የሚነሱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለመመርመር የአፍሪካ ህብረት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር በጋራ ምርመራዎችን እንዲያካሂድ መንግስት ያለውን ፍላጎት መገለጹን አንስተዋል።

በሌላ በኩል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚመለከታቸው አካላት በጋራ ምርመራ ለማድረግ በመንግስት በኩል ያለውን ዝግጁነት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጻቸውን አቶ ደመቀ አብራርተዋል።

አምባሳደር ኢቨግኒ ታሪኪንን በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ሁሉን አቀፍ ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

የተፈረሙ ስምምነቶችን ወደ ስራ በማስገባት እንዲሁም በሂደት ያሉ ስምምነቶች እንዲፈረሙ በማድረግ በሀገራቱ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ትብብር የበለጠ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ በውይይቱ መግባባት ላይ ተደርሷል ተብሏል።

አቶ ደመቀ በኢትዮጵያ እና ሩስያ መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ ግንኙነት አውስተው፤ በቀጣይም ሁለቱ ሀገራት በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን መድረኮች ያላቸውን ትብብር የበለጠ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.