Fana: At a Speed of Life!

አዲሱ መንግስት የገባዉን ቃል ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅበታል-ምሁራን

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 3፣2014 (ኤፍ ቢሲ) አዲስ የተመሰረተው መንግስት ለውጥ አካታች ብሄራዊ የውይይት መድረክ በማካሄድ አንድነቷ እና ህልዉናዋ የተጠበቀ ጠንካራ ሀገር ለትውልድ ለማስተላለፍ የገባውን ቃል በተግባር ሊያዉል እንደሚገባ ምሁራን ተናገሩ፡፡
ከፋና ብሮድ ካሰቲነግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ ረዳት ፕሮፌሰር ዳምጠው ተሰማ እንደገለፁት፥ ተፎካካሪ ፓርቲዎችን ጭምር አካታች ሆኖ የተዋቀረው መንግስት የሀገር ህልውናን ማስጠበቅን ቀዳሚ ስራው ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።
በዚሁ ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህሩ ሙሉቀን ይታይህ በበኩላቸው፥ የተራዘመ ጦርነት የሚያስከትለው ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመት ከፍተኛ በመሆኑ አዲሱ መንግስት የህወሓትን የጥፋት ቡድን ሩጫ በመግታት የህግ የበላይነትን በማስከበር አፋጣኝ እርምጃ ሊወስድ እንደሚገባ ተናግረዋል።
የጎንደር ዩኒቨርሲቲው የፖለቲካል ሳይንስ መምህሩ ረዳት ፕሮፌሰር አንዳርጋቸው ተስፋሁን በበኩላቸዉ ፥ወጣቶች እና የተማረው ክፍል በተቻለው መጠን በሀገሩ ጉዳይ ላይ ተሳታፊ እንዲሆን ማበረታታት እና ዜጎችን በችሎታቸው ብቻ መዝኖ በስራ ላይ ማሰማራት የነበሩ ችግሮችን ከማቅለል አንጻር አበርክቶው ከፍተኛ ነው ብለዋል።
ከመንግስት፤መገናኛ ብዙሃን፤ከህብረተሰብ ክፍሎች እና የማህበረሰብ አንቂዎች አንድነትን በማስተማር ረገድ ትልቅ ሚና ይጠበቃል ያሉት ደግሞ የእንጂባራ ዩኒቨርሲቲ መምህሩ ስማቸው አማረ ናቸዉ፡፡
ኢትዮጵያ ምርጫ አካሂዳ በሕዝብ የተመረጠ አዲስ መንግስት ብትመሰርትም ዛሬም የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጫና አይሏል የሚሉት ምሁራኑ፥ የአሜሪካን እና የምዕራባውያን ሃገራትን ጫና ለመቋቋም በእውቀትና በብስለት ላይ የተመሰረተ የዲፕሎማሲ አካሄድን መከተል ከአዲሱ መንግስት ይጠበቃል ብለዋል።
በወታደራዊውም ሆነ በፖለቲካው ረገድ የተቀናጀ እና የተደራጀ ስራ መስራት እንደሚያስፈልግም ያሳሰቡ ሲሆን ከዚህ ባሻገር ህዝቡ የኋላ ደጀንነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥልና የህልውና ዘመቻው በአጠረ ጊዜ እንዲቋጭ ንቅናቄ መፍጠር ላይ መንግስት ትልቅ የቤት ስራ እንዳለበት ነው ምሁራኑ የተናገሩት።
በሰላም አሰፋ እና አፈወርቅ አለሙ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of 1 person and standing
0
People Reached
0
Engagements
Distribution Score
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.