Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና እስራኤል በፋርማሲዩቲካል እና አይሲቲ ዘርፍ በጋራ መስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳንዶካን ደበበ በኢትዮጵያ እና ብሩንዲ የእስራኤል አምባሳደር ራፋኤል ሞራቭ ጋር ሁለቱ ሀገራት በኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጅ እና በፋርማሲዩቲካል ዘርፍ አብሮ መስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ አቶ ሳንዶካን ኢትዮጵያ በኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጅ እና በፋርማሲዩቲካል ዘርፍ ዓለም አቀፍ ባለኃብቶችን በመሳብ ላይ እንደምትገኝ ገልፀዋል፡፡
በዚህም እስራኤል በዘርፎቹ ያላት ልምድ ውጤታማ ሊያደርግ የሚችል በመሆኑ የሃገሪቱን ባለኃብቶች ወደ ስራ በማስገባቱ ረገድ እና የሚያጋጥሙ ችግሮችን በጋራ በመፍታት አብሮ መስራት እንደሚያስፈልግ ገልፀው የእስራኤል ባለሃብቶች መጥተው መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በእስራኤል ሀገር የሚገኙ የአይሲቲ ፓርኮች ከኢትዮጵያ አይሲቲ ፓርክ ጋር የእህትማማች ግንኙነት በመፍጠርም ልምድ በመለዋወጥ እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመማማር በጋራ መቀጠል በሚቻልበት ጉዳይ ላይም የእስራኤል ኤምባሲ በትኩረት እንዲመለከተው ዋና ስራ አስፈፃሚው ጠይቀዋል፡፡
በኢትዮጵያ እና ብሩንዲ የእስራኤል አምባሳደር ራፋኤል ሞራቭ በበኩላቸው በእስራኤል የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባለሃብቶችን ወደ ስራ ለማስገባት ጥረት እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው፥ ይህንኑ ተግባር አጠናክሮ በማስቀጠል የእስራኤል ባለኃብቶች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው እንዲያለሙ ይሰራል ብለዋል፡፡
አምባሳደር ራፋኤል ሞራቭ የእስራኤል ባለሃብቶች በአይሲቲ እና በፋርማሲዩቲካል ምርት ላይ በስፋት መስራት እንደሚፈልጉ አንስተው ከዚህ ባሻገር ለሁለቱ ዘርፎች ቅድሚያ ቢሰጥም በቀጣይ በሶላር ኢነርጂ እና በጂኦተርማል ኢነርጂ ዘርፍ አብሮ መስራት እንደሚቻል አምባሳደሩ መግለፃቸውን ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ያገኘ ነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.