Fana: At a Speed of Life!

በኪጋሊ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሕንጻ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ በሩዋንዳ ኪጋሊ ለኢትዮጵያ ኤምባሲ ጽሕፈት ቤት ግንባታ የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ፡፡

ግንባታው የሚከናወነው በ7 ሺህ 771 ካሬ ሜትር ላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡

አምባሳደር ታዬ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት÷ በኪጋሊ የተበረከተው መሬት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የበለጠ ፍሬያማ እንዲሆን የሚረዳ ነው።

ኢትዮጵያም ለሩዋንዳ ኤምባሲ መገንቢያ በአዲስ አበባ ተመሳሳይ መጠን ያለው መሬት መስጠቷን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያና ሩዋንዳ መካከል ከፈረንጆቹ 2012 ጀምሮ 23 ስምምነቶች እና የመግባቢያ ሰነዶች መፈረማቸውን በመግለጽ÷ እነዚህን ወደ ውጤት ለማስገባት የኤምባሲ ጽሕፈት ቤት ግንባታ ቁልፍ ሚና አለው ብለዋል።

ሀገራቱ ከሁለትዮሽ ባለፈ በዓለም አቀፍ የትብብር መድረኮች አቋማቸውን በኅብረት የሚያራምዱ መሆናቸውንም አንስተዋል፡፡

ሩዋንዳ ከቅኝ ግዛት ለመውጣት ባደረገችው ተጋድሎ ወቅትም ሆነ ከአስከፊው ዘር ጭፍጨፋ በኋላ ኢትዮጵያ ቀድማ በመድረስ ለሩዋንዳውያን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጓ ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.