Fana: At a Speed of Life!

በኤፍ ኤም 98.1 ለአድማጭ የሚደርሰው ‘የጨረቃ ውል’ ድራማ 100ኛ ክፍል ዛሬ ለአየር በቅቷል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፋና ኤፍ ኤም 98.1 ቅዳሜ ከረፋዱ 5 እስከ 9 ሠዓት ለአድማጭ በሚደርሰው ‘ማረፊያ’ የመዝናኛ ፕሮግራም ውስጥ የሚገኘው ‘የጨረቃ ውል’ ድራማ ዛሬ ክፍል 100 ለአየር በቅቷል፡፡

የድራማውን 100ኛ ክፍል ለአየር መብቃት አስመልክቶ ልዩ ዝግጅት ተካሂዷል፡፡

የፋና ኤፍ ኤም 98.1 የሬዲዮ ፕሮግራሞች ዳይሬክተር አዳም ታደሰ በዝግጅቱ ላይ ባደረገው ንግግር÷ ድራማው በአፃፃፉና አቀራረቡ የራሱን ቀለም መፍጠሩን አንስቷል፡፡

በቀጣይም የተሰጡ ገንቢ አስተያየቶችን በመጠቀም በተሻለ ይዘት ድራማው ዳብሮ እንደሚቀጥል አመላክቷል፡፡

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትም በሬድዮ መዝናኛ ዝግጅቶቹ አድማጩን የሚመጥን ይዘት በይበልጥ ለማቅረብ በትጋት እየሠራ መሆኑን አስረድቷል፡፡

በ ‘የጨረቃ ውል’ ድራማ የጋሽ ቦሎ ገፀ-ባህሪን ወክሎ  የሚጫወተው በፍቃዱ ከበደ÷ ድራማው ልዩ መሆኑን ገልጾ እስከዛሬ ከተጫወታቸው ሁሉ ደስብሎት የሚሠራው መሆኑን ተናግሯል፡፡

የድራማው አዘጋጅ ዮናስ አብርሃም በበኩሉ÷ ዛሬ 100ኛ ክፍሉ ላይ የደረሰው ‘የጨረቃ ውል’ ከሬድዮ ድራማነት በላይ የሬዲዮ ቴአትር መሆኑን ገልጿል፡፡

ባለታሪኮቹ  ከሕዝብ ጋር የሚኖሩ ስለሆኑ የማኅበረሰቡ የሕይወት ነፀብራቅ ናቸውም ብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.