Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ከአረብ አገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር የሁልጊዜ ፍላጎቷ ነው -ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የአረብ ሀገራት አምባሳደሮች ምክር ቤት አባላትና የአረብ ሊግ አምባሳደር በጠየቁት መሠረት በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋቸዋል::

በውይይቱ የአምባሳደሮቹ ዲን፥ ቡድኑ በሚወክሏቸው አገሮችና በኢትዮጵያ መካከል በምክክርና በመግባባት ላይ የተመሰረተውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል::

ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ፥ አረብ አገራት የኢትዮጵያ ጎረቤት በመሆናቸው ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ሁልጊዜም ፍላጎቷና ጥረቷ እንደሆነ እና የአረብ ሊግ አባል የሆኑ የአፍሪካ አገሮች ጠንካራ ድልድይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

“ፈጣሪ የሰጠን በርካታ የተፈጥሮ ሃብት ለሁላችንም የሚበቃ እንደመሆኑ ማንኛውንም ጉዳይ በየቀጠናዎቻችን መፍታት ይገባል” ሲሉ መናገራቸውን ከፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.