Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ 17ኛውን የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ አዘጋጅነቷን ከፖላንድ በይፋ ተረከበች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በፖላንድ አዘጋጅነት ሲካሄድ የነበረው 16ኛው የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ ተጠናቋል።

በጉባኤው ማጠናቀቂያ በ2015 የሚካሄደውን 17ኛውን የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ ለማስተናገድ ኢትዮጵያ ከፖላንድ በይፋ ተረክባለች።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ÷ በቀጣይ ዓመት ኢትዮጵያ የምታስተናግደው ፎረም የአፍሪካውያንን የኢንተርኔትና የመሰረተ ልማት ችግሮችን በመቅረፍ ካደጉት አገራት ተርታ የሚያሰልፋትን አቅም ለመፍጠር የመፍትሄ አቅጣጫዎች የሚጠቆሙበት እንዲሆን እንሰራለን ብለዋል።

የዘንድሮው ጉባኤ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን የተጋፈጥንበትና በወረርሽኙ ምክንያት የዲጂታል ቴክኖሎጂ አማራጮች የተሻሉ ሆነው የተገኙበት ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ ፥ የዲጂታል አስቻይ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ፖሊሲ አውጭዎችና ባለድርሻ አካላት በትኩረት መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።

የመሰረተ ልማት ግንባታ ችግር ለአፍሪካ የመጪው ጊዜ ፈተና ሊሆን እንደሚችል ስጋታቸውንም ገልፀው ÷ ኢትዮጵያ 17ኛው የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባዔ በስኬት ለማጠናቀቅ ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

በቀጣይ ዓመት በኢትዮጵያ የሚካሄደው የኢንተርኔት አስተዳደር ፎረም የአፍሪካ ጉዳይ ጎልቶ እንዲወጣ ይሰራል መባሉን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.