Fana: At a Speed of Life!

ከተማ አስተዳደሩ እና የኢትዮጵያ ካቶሊከዊት ቤተክርስቲያን የ510 ሚሊየን ብር ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ ፣ግንቦት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረስብከት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የ510 ሚሊየን ብር ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ ለማድረግ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ስምምነቱን ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና የኢትዮጵያ ካቶሊከዊት ቤተክርስቲያን ካርዲናል ብርሃነ እየሱስ ሱራፌል  ተፈራርመዋል ።

በአዲስ አበባ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር በከተማ አስተዳደሩ ጥረት ብቻ  መፍታት እንደማይቻል የገለፁት ምክትል ከንቲባ ዋ÷ ቤተክርስቲያኗ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የኅብረተሰብ ክፍሎች ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግራቸውን ለመቅረፍ የጀመረችውን ስራ አጠናክራ መቀጠል አለባት ብለዋል፡፡

ቤተክርስቲያኗ በከተማው ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የኅብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ለማድረግ ለያዘችው እቅድ በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ካርዲናል ብርሃነ እየሱስ ሱራፌል በበኩላቸው÷ የከተማ አስተዳደሩ ከተማሪዎች ጀምሮ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ የሚገኙ  ዜጎችን ለመመገብ የጀመራቸውን ስራዎች የሚያስመሰግነው መሆኑን ገልጸዋል ።

በትብብር የሚሰሩት ስራዎች በአጠቃላይ 510 ሚሊየን ብር ወጪ የሚደረግባቸው ሲሆን በቀን 150ሺህ ዳቦ የማምረት አቅም ያለው የዳቦ ማምረቻ፣ የትምህርትን ሽፋንና ጥራት በማረጋገጥ የሚያግዙ 8 የመዋለ ህጻናት፣ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን እና የቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጅ ግንባታ፣ የተለያዩ የሥራ ዕድል ፈጠራን የሚያግዙ የክህሎት ስልጠናዎች የሚሰጡበት የወጣቶች ሁለገብ ማዕከል ሥራ እንደሚገኙበት ስምምነቱ ላይ መገለጹን ከከተማ አስተዳደሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.