Fana: At a Speed of Life!

ከትራፊክ አደጋ የፀዳ የትራንስፖርት አገልግሎት ለሃገራዊ ህዳሴ በሚል መሪ ቃል የእግር ጉዞ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2012 (ኤፍቢሲ) ከትራፊክ አደጋ የፀዳ የትራንስፖርት አገልግሎት ለሃገራዊ ህዳሴ በሚል መሪ ቃል የእግር ጉዞ ተደረገ።

በዛሬው ዕለት ከሀረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትራንስፖርትና መንገድ ቢሮ እንዲሁም ትምህርት ቢሮ ጋር በመሆን የእግር ጉዞ ተደርጓል።

የሀረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትራንስፖርትና መንገድ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አብዲ ሌማይ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊው አቶ ሙክታር ሳቢህ የእግር ጉዞ መርሃ ግብሩን አስጀምረዋል።

በመርሃ ግብሩ ግንዛቤ ያለውና የኔነት ስሜቱ የጎለበተ ማህበረሰብን ለመፍጠር ሁሉም ሃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ ጥሪ መቅረቡን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የትራንስፖርት ሚኒስቴር በያዝነው በጀት ዓመት በመንገድ ደህንነት ዙሪያ ሰፊ የንቅናቄ ስራዎችን እያከናወነ ሲሆን መርሃ ግብሩ በተለያዩ የክልል ከተሞች እየተከናወኑ ለሚገኙ የንቅናቄ መድረኮች ማሳያ መሆኑ ተገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.