Fana: At a Speed of Life!

‘ከጽንፎች መሐል ወርቃማውን አማካይ ፍለጋ’ በሚል ርእስ የአዲስ ወግ ዐቢይ ጉዳይ ሦስተኛ ክፍለ ጊዜ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ‘ከጽንፎች መሐል ወርቃማውን አማካይ ፍለጋ’ በሚል ርዕስ የአዲስ ወግ ዐቢይ ጉዳይ ሦስተኛው ክፍለ ጊዜ ጽንፈኝነትን የመከላከል ርምጃዎች ላይ አተኩሮ እየተካሄደ ነው።

ከብልጽግና ፓርቲ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ፣ የሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ አንዷለም እንዲሁም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔረዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በሀሳብ አቅራቢነት መሳተፋቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ በልጅጌ ፥ “የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከጽንፈኝነት እንዲላቀቅ የሀሳብ ሽግግር ማድረግ ወሳኝ ነው ፥ ወደ ክርክር ከማዘንበል ውይይትን መርጦ ሁሉን አካታች ምክክር ማድረግ ያስፈልጋል” ብለዋል።

ከብዝሃነታችን አኳያ ወንድማማችነት ላይ ያተኮረ ሥራ መሥራት ይጠበቅብናል ሲሉም ነው የገለጹት።

የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዷለም ፥ “ሰላምን የማምጣት ሥራ ከለውጡ አንስቶ ትኩረት ተሰጥቶበታል ፤ ጽንፈኝነትን ለማስቀረት ብዝሀነትን ለመቀበል የሚያስችሉ ሰፊ ሥራዎች ተሰርተዋል” ብለዋል።

ታሪክን የምንመለከትበትን መንገድ ከትናንት ጠቃሚውን ወስዶ የማይጠቅመውን መተው ላይ ማተኮር እንደሚገባ ያነሱት ሚኒስትሩ ፥ ገለልተኛ ተቋማትን እና የጸጥታ አካላትን የማጠናከር ሰፊ ሥራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.