Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽኑ በደብረ ብርሃን ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን በደብረ ብርሃን ከተማ ተፈናቅለው ለሚገኙ ወገኖች ከ26 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸውን የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡
የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ አሸባሪውን ቡድን ለማጥፋት ከሚፋለሙ ጐን ለጐን በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖችን አለንላችሁ ማለት አስፈላጊ በመሆኑ ነው ድጋፉን ያደረግነው ብለዋል፡፡
ድጋፉም አልባሳት እና ምግቦችን ያካተተ መሆኑን ጠቁመው÷ አጠቃላይ ግምቱም 26 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ከችግሩ አንፃር የተደረገው ድጋፍ በቂ ባለመሆኑ÷ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
ድጋፉ ላይ የተገኙት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጐጌ ተስፋዬ በበኩላቸው÷ ህወሓት በሰው ልጆች ላይ እያደረሰ ያለው አረመኔያዊ ድርጊት ዘርፈ ብዙ ቀውሶችን ያስከተለ በመሆኑ ይህን ለማለፍ መደጋገፍ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የሰሜን ሸዋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ወ/አማኑኤል÷ በዚህ ወቅት ለተፈናቀሉ ወገኖች ኮሚሽኑ ላደረገው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡
በኢትዮጵያዉያን ወትሮም ቢሆን ከተደጋገፉ ማለፍ የማይችሉት እንደሌለም ነው አቶ ሲሳይ የተናገሩት፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን ከዚህ ቀደምም የ53 ሚሊየን ብር ድጋፍ ለዞኑ ማስረከቡ የሚታወስ ነው፡፡
በዛሬው ድጋፍ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩን ዶ/ር በለጠ ሞላን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮችም ተገኝተዋል፡፡
በአይናለም ስለሺ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.