Fana: At a Speed of Life!

ኮሚቴው በትግራይ ክልል በግጭት ለተጎዱ 15 ሺህ አርሶ አደሮች የምርጥ ዘር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚያካሂደውን የሰብል ምርጥ ዘር ስርጭት በመቀጠል በትግራይ ክልል በግጭቱ ለተጎዱ 15 ሺህ አርሶ አደር አባወራዎች ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፍ የተደረገላቸው አርሶ አደሮች በትግራይ ክልል በላዕላይ ማይጨው ከሚገኙ ስምንት ቀበሌዎች እና በማዕከላዊ ትግራይ ዞን በአድዋ ወረዳ ከሚገኙ አራት ቀበሌዎች የመጡ ናቸው ተብሏል።

በዚህም ኮሚቴው ለእያንዳንዱ ቤተሰብ 10 ኪሎ ግራም የጤፍ ዘር እና 2 ነጥብ 5 ኪሎ ግራም የማሽላ ዘር ድጋፍ ማድረጉን ከዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.