Fana: At a Speed of Life!

ዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ፍትሃዊና ሚዛናዊ የሆነ ድጋፍ ሊያደርግ ይገባል – አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በትክክል በመገዘብ ዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ፍትሃዊ እና ሚዛናዊ የሆነ ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጥሪ አቀረቡ።

አቶ ደመቀ ከአየርላንድ የውጭ ጉዳይ እና መከላከያ ሚኒስትር ስምዖን ኮቨኒ ጋር በኒውዮርክ ተገናኝተው መክረዋል።

በሰሜን የሃገሪቱ ክፍል ህውሓት አጠናክሮ የቀጠለባቸውን እኩይ ጥፋት እና ጥቃቶችን ተከትሎ፤ በመንግስት በኩል በሚወሰዱ እርምጃዎች ላይ በተደጋጋሚ የሚቀርቡ ክሶች መነሻቸው የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ በትክክል ካለመረዳት የመነጨ ነው ሲሉ አቶ ደመቀ ገልጸዋል።

የህውሓት ጥፉት የወራት ዕድሜ መነፅር ብቻ የሚመዘን ሳይሆን ባለፉት ዓመታት በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በርካታ ዜጎች ሞት ጀርባ ምክንያት የነበሩ አሸባሪዎችን ሲያደራጅ፣ ሲደግፍ እና ስምሪት ሲሰጥ እንደነበር በዝርዝር አብራርተዋል።

መንግስት በሃገር ሉዑዓላዊነት ጉዳይ እና የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ በሚወስዳቸው ህጋዊ እርምጃዎች ዙሪያ ሚዛናዊነት በጎደለው አግባብ መረዳት ኢትዮጵያ ውስጥ ካለው ነባራዊ እውነታ መሸሽ እንደሆነ ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ ችግሮች ዙሪያ ዓለምአቀፉ ማህበረሰብ እንዲሁም በሁሉም ወዳጅ ሀገራት እይታ ዘንድ ፍትሃዊ እና ሚዛናዊ የሆነ ግንዛቤ እንዲያዝ እንፈልጋለን ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

መንግስት በሃላፊነት ስሜት የሚወስዳቸውን የሰላም አማራጮች እና ህጋዊ እርምጃዎች ተከትሎ ተደጋጋሚ ክሶች መቅረባቸውን ጠቁመዋል።

እንደ አቶ ደመቀ ገለፃ በተደጋጋሚ የሚቀርቡት ክሶቹ ተቀባይነት የሌላቸው እና በሃገራት መካከል ያለውን ግንኙነት የሚጎዱ ናቸው።

በመጨረሻም የአየርላንድ መንግስት ስለኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ የሰጠውን ትኩረት በማድነቅ የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ በትክክል በመገንዘብ ዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ፍትሃዊ እና ሚዛናዊ የሆነ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ማቅረባቸውን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.