Fana: At a Speed of Life!

የሃይማኖቶችን የመቻቻልና አብሮ የመኖር ባህል የሚፃረሩ ጽንፈኛ አካሄዶችን አወግዛለሁ –  ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሃይማኖቶችን የመቻቻልና አብሮ የመኖር ባህል የሚፃረሩ ጽንፈኛ አካሄዶችን እንደሚያወግዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ትናንት በአማራ ክልል በሞጣ ከተማ ቤተክርስቲያንና መስጊዶች መቃጠላቸውን ተከትሎ በፌስቡክ ገጻቸው  ድርጊቱን ያወገዙበተን መግለጫ አወጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው  “በብልጽግና ጎዳና ላይ በምትገኘው ኢትዮጵያ የሀገራችንን የቆየ የሃይማኖቶችን የመቻቻልና አብሮ የመኖር ባህል የሚፃረሩ ጽንፈኛ አካሄዶች ቦታ የላቸውም፤ እንዲህ ያሉ የፈሪ አካሄዶችን አጥብቄ አወግዛለሁ” ብለዋል።

መላው ሰላም ወዳድ ኢትዮጵያውያንም የመከባበርና አብሮ የመኖር ጥልቅ እውቀታቸውን እንዲያጋሩም ጥሪ አቅርበዋል።

“ከፋፋይ አጀንዳዎችን መረዳትና መጠየፍ የጋራ ዕድገታችንን ለማረጋገጥ ያስችላል” ሲሉም መልእክት አስተላልፈዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.