Fana: At a Speed of Life!

የሚስተዋለውን ግጭት እና አለመረጋጋት ለመፍታት የሀይማኖት መሪዎች፣ መንግስት እና ምዕመናን ሊሰሩ ይገባል – ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እየተስተዋለ ያለውን ግጭት እና አለመረጋጋት ለመፍታት የሀይማኖት መሪዎች፣ መንግስት እና ምዕመናን ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፅዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጥሪ አቀረቡ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ መደበኛ ጉባኤ እየተካሄደ ነው፡፡

ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ በሃገሪቱ የሚስተዋሉ ግጭቶች እና አለመግባባቶች በርካታ ጉዳት እያደረሱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ አንጻርም ልዩነቶችን በውይይት በመፍታት እርቅን ማስፈን እና ዘላቂ ሰላምን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል፡፡

በንግግራቸው የአክራሪዎችና የተቃራኒዎች እንቅስቃሴ ቤተ ክርስቲያኗን የገጠሟት ችግሮች መሆናቸውንም አንስተዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ውስጣዊ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ፈተና መሆናቸውን ጠቅሰው ጉባኤው እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ሊሰራ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በመታገስ አየልኝ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.