Fana: At a Speed of Life!

የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ከሀሰተኛ መረጃዎች ራሳቸውን እንዴት መጠበቅ ይችላሉ?

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀሰተኛ መረጃዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እበዙ እና እየረቀቁ እንደሚገኙ የሚታወቅ ሲሆን ፥ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ከእነዚህ መረጃዎች ራሳቸውን እንዴት መጠበቅ እንደሚችሉ እንመለከታለን፡፡

የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ከሀሰተኛ መረጃዎች ራሳቸውን እንዴት መጠበቅ ይችላሉ?

– መረጃውን ያስተላለፈው አካል ማነው? የኋላ ታሪኩስ ምን ነበር? ብሎ መጠየቅ፡- ይህ የመረጃ አስተላላፊውን አቋም ከግምት ውስጥ በማስገባት ስለመረጃው ትክክለኛነት የግል አስተያየትና ተጨማሪ ማረጋጋጫ ለመፈለግ ያግዛል።

– መረጃው የተለቀቀበት ትክክለኛ ቀን እና ሰዓት መቼ ነው? የሚለውን ማጣራት፡- አንዳንድ መረጃዎች ቀደም ብለው የተለቀቁ ሆነው እንደ አዲስ በድጋሜ የሚወጡ ከሆነ በእርግጥም የተለቀቁት መች እንደነበር ማረጋገጥ ተገቢ ነው፤

– ርዕሰ ዜናው/ ርዕሰ አንቀፁ እና በስሩ የሚገኙ ማብራሪያዎች ተመሳሳይነትን ማረጋገጥ፡- አንዳንድ ርዕሶችና መረጃዎቹ የሚለያዩ ሊሆኑ ይችላሉ፤ ርዕሶች የመረጃ ተቀባዩን ትኩረት ለመሳብ ብቻ ተዘጋጅተው ከአባሪው መረጃ ጋር የተለያዩ ሊሆኑ ስለሚችሉ መሉ መረጃን ማንበብ ወይም ማድመጥ ተገቢ ነው።

– በምንጭነት የተጠቀሰ ምንጭ ወይም አባሪ የጠቀሰ ከሆነ ማንነት እና ምንነቱን ማረጋገጥ፡- መረጃዎች እንደምንጭነት የጠቀሱትን አካልም ይሁን አባሪ በራሱ በድጋሜ እውነተኛ መረጃ መሆኑን ማረጋገጥ፤

– በድጋሜ ማጣራትን ተግባራዊ ማድረግ፡- መረጃው በተደጋጋሚ እና በታማኝ ምንጮችም የተረጋገጠ መሆኑን ማረጋገጥ፤

– ጥያቄ የሚያስነሱ እና የሚያጠራጥሩ ፎቶዎች ወይም ጥቅሶችን መጠራጠር እና ስለ እውነተኛነታቸው ተጨማሪ ማጣራት ማድረግ፤

– ወገንተኝነትን ማስወገድ፡ -መረጃዎችን እኛ የምንፈልጋቸው ዓይነት ብቻ ስለሆኑ ማመን ፥ የማንፈልጋቸው ሲሆኑ ደግሞ አለማመንን ብቻ ከመምረጥ መቆጠብ፤

– የመረጃ ማጣሪያ መሳሪያዎች ወይም ግብዓቶችን ን ጥቅም ላይ ማዋል፡- የተለያዩ የምስል ትክክለኛነትን የሚያጣሩ የ“ፋክት ቼክ” ቱሎችን ተጠቅሞ ከመረጃው ጋር የተያያዙ ምስሎች ትክክለኛነት ማጣራት።

ለምሳሌ- ፎቶዎቹ ፎቶ ሾፕድ የሆኑ ወይም በሌላ ቦታና ሁኔታ ጥቅም ላይ ውሎ በድጋሜ ለሀሰተኛ ማስረጃነት ጥቅም ላይ የዋለ ከሆነ በሰርች ኢንጅን ለምሳሌ “የጎግል ሪቨርስ ኢሜጅ ሰርች” (Google Reverse Image Search)፣

በዌብሳይት ለምሳሌ- “ፎቶ ፎረንሲክ” (FotoForensics) ወይም “ቲን አይ” (TinEye) አሊያም

በአፕሊኬሽን ለምሳሌ- “ትሩ ፒክ” (Truepic) ወይም “findexif” የመሳሰሉ እና ሌሎች በርካታ ዘዴዎችን በመጠቀም ስለ ምስሉ ተገቢ መረጃን በመሰብስብ ስለ ተያያዥነቱ ማጣራት እንዲሁም ሀሰተኛ ተንቀሳቃሽ ምስሎች (ዲፕ ፌክ) የሆኑ መረጃዎችን በጥንቃቄ መመልከት እና ያልተለመዱ እና ተፈጥሯዊ ያልሆኑ እንቅስቃሴዎችን በመመልከት ሀሰተኛ መሆኑን እና አለመሆኑን ማረጋገጥ ተገቢ ነው።

– መረጃዎችን ከተገቢ ምላሽ ሰጪ አካል፣ ከቦታው ካለ አካል ማጣራት እና የግል ሚዛናዊነት እጅግ ወሳኝ ሚና እንዳላቸው ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.