Fana: At a Speed of Life!

የምስራቅ ኢትዮጵያ አጎራባች ክልሎች ገለልተኛ የመንግሥት ተቋማት በሚፈጠርበት ሁኔታ በጅግጅጋ ከተማ እየመከሩ ነው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ ኢትዮጵያ አጎራባች ክልሎች ገለልተኛና ከፖለቲካ ነጻ የሆኑ የህዝብ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት በሚፈጠርበት ሁኔታ የሚወያዩበት መድረክ በሶማሌ ክልል ርዕሰ መዲና በጅግጅጋ ከተማ ተጀመረ።

በምክክር መድረኩ ላይ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንና የሰላም ሚኒስቴር ሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የሶማሌ ፣ የኦሮሚያ፣ የሀረር፣ የአፋርና የድሬዳዋ አስተዳደር የሲቪል ሰርቪስና ሰው ሃይል ልማት ቢሮ ኃላፊዎች እንዲሁም ከምስራቅ ኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ምሁራን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የሶማሌ ክልል የሲቪል ሰርቪስና ሰው ሃይል ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዲቃድር ረሺድ ውይይቱ የመንግሥትና የህዝብ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ለዜጎች ተገቢና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡ በህዝብ አገልግሎት አሰራር ሥርዓቶች ላይ ያሉ ችግሮች በአስቸኳይ እንዲቀረፉና አዳዲስና ዘመናዊ የህዝብና መንግሥት አገልግሎት አሰራሮችን ለመዘርጋት ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።

መድረኩ ዜጎች በመንግሥት ተቋም አገልግሎት አሰጣጥ እርካታ እንዲኖራቸው፣ የህዝብ አገልግሎት አሰራሮች ዘመናዊ በሚሆኑበትና ቀልጣፋ የአገልግሎትና አሰራር በሚፈጠርበት ሁኔታ ላይ ትኩረት እንደሚያደርግም ተናግረዋል።
የምክክር መድረኩ ለሶስት ቀናት ያእንደሚቆይ ከሶማሌ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዪች ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.